ስለዚህ መፅሃፍ

በሕይወት ውስጥ ብዙ ዕድሎች የሚከፈቱት ሀሳቡን በግልጽና በልበ ሙሉነት ለሚያቀርብ ሰው ነው፤ ለምሳሌ በሥራ ቃለ-መጠይቅ፣ በስብሰባ፣ በሠርግና በምረቃ መድረክ፣ ወይም በካሜራ ፊት። ግን ብዙዎቻችን ድንቅ ሀሳብ ይዘን በፍርሃት ምክንያት ዝም እንላለን።

"የንግግር ጥበብ — ሃሳብን የማሸነፍ ሚስጥር" ይህንን ፍርሃት ወደ ጉልበት እንድትቀይር የሚረዳ ተግባራዊ መመሪያ ነው። የንድፈ ሐሳብ ክምር አይደለም፤ ነገ ጠዋት በሥራ ቦታህ ወይም በማኅበራዊ ሕይወትህ ልትጠቀምበት የምትችል መሣሪያ ነው።

በዚህ መጽሐፍ ውስጥ የምትማረው፦

  • የመድረክ ድንጋጤን በሳይንሳዊ ዘዴዎች ማሸነፍ (የ4-7-8 አተነፋፈስ፣ የዓይነ ሕሊና ልምምድ)
  • የአድማጭን ማንነት መረዳት እና ንግግርን በ"የሦስቱ ሕግ" ማዋቀር
  • በታሪክ አነጋገር (Storytelling) የሰዎችን ልብ መማረክ
  • ድምፅን፣ ዝምታንና የአካል ቋንቋን እንደ መሣሪያ መጠቀም
  • የአርስቶትል የማሳመን ምሰሶዎች፦ ኤቶስ፣ ፓቶስና ሎጎስ
  • አስቸጋሪ ጥያቄዎችን በPREP ቀመር መመለስ
  • ሳትዘጋጅ ድንገት ስትጠየቅ በልበ ሙሉነት መናገር
  • ለሥራ ስብሰባ፣ ለሠርግ፣ ለምረቃ፣ ለካሜራና ለማኅበራዊ ሚዲያ የሚሆኑ ንግግሮች

በዚህ ሦስተኛ እትም ውስጥ የተጨመሩት፦

  • ሙሉ የቋንቋና የፊደል እርማት
  • በየምዕራፉ መጨረሻ ማጠቃለያዎችና የማሰላሰያ ጥያቄዎች
  • የንግግር ዝግጅት ማረጋገጫ ዝርዝር እና የ30 ቀን የልምምድ ዕቅድ
  • የራስ-ግምገማ ቅጽ፣ የንግግር ካርታ ቅጽና የቃላት መፍቻ

ተማሪ፣ የሥራ መሪ፣ ነጋዴ፣ መምህር ወይም ይዘት ፈጣሪ ብትሆን፣ ይህ መጽሐፍ ድምፅህን ለዓለም እንድታሰማ ይረዳሃል።

ምን ያገኛሉ?

  • 232 ገጾች · 21 ምዕራፎች · 5 አባሪዎች
  • የተግባር ልምምዶችና የምዕራፍ ማጠቃለያዎች
  • የ30 ቀን የልምምድ ዕቅድና የራስ-ግምገማ ቅጽ
  • ፒዲኤፍ — ከክፍያ በኋላ ወዲያው ይወርዳል
የንግግር ጥበብ499 ብር

ተጨማሪ ከ ቀለም

ሁሉንም ይዩ
የንግግር ጥበብ499 ብር